ኒዩትሪሽን ፎር ኤዱኬሽን ኤንድ ዴቨሎፕመንት (Nutrition 4 Education & Development – N4ED): ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል

ኒዩትሪሽን ፎር ኤዱኬሽን ኤንድ ዴቨሎፕመንት (Nutrition 4 Education & Development – N4ED) የተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት ከነሀሴ 26 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ በላይሰንስ ቁጥር 3687 በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጀንሲ ተመዝግቦ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።

ድርጅቱ በየዓመቱ በሰኔ 30 ሂሳቡን የሚዘጋ ሲሆን፣ የ2011 ዓ.ም የድርጅቱን ሒሳብ በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ለመጫረት የምትፈልጉ የኦዲት ድርጅቶች (Audit firms) ከዚህ በታች የተጠቀሱት በማሟላት እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።

ሀ. የኦዲተር የሙያ ማረጋገጫ፣

ለ. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣

ሐ. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ መረጃ፣

መ. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣

ሠ. የተጨማሪ እሴት ታክስ   (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣

ረ. ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ (A.A.B.E) ፈቃድ፣

ለመጫረት የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች የምትሰሩበትን ዋጋና የሚያስፈልገውን የጊዜ መጠን የሚገልጽ ፕሮፖዛል በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጋችሁ በመካኒሳ አቦ ማዞሪያ አካባቢ በሚገኘው ቢሮአችን ይህ ማስታወቂያ በወጣበት በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ ።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0966784304 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ኒዩትሪሽን ፎር ኤዱኬሽን ኤንድ ዴቨሎፕመንት