የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2013
ነጌሌ አርሲ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ለነጌሌ አርሲ ከተማ ሴክተር መ/ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
- የፅዳት እቃዎች
- የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ሞተር ሳይክሎች፣
- የደንብ ልብሶች፣
- የስፖርት ትጥቆች፣
- የመኪና ጎማዎች እና የቴክኒክና ሙያ የሥልጠና ማቴሪያሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ለመወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች፡-
- የ2011 ዓም ግብር የከፈለና የ2012 ዓ.ም የንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝገቢ የሆነ ፤
- ህጋዊ የአቅራቢነት ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ፤
- አሸናፊው ድርጅት የእቃውን ናሙና ማቅረብ የሚችል፤
- ለጨረታው ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች ማሻሻል፣ መቀየር እንዲሁም ሃሳቡን እቀይራለሁ ማለት አይችልም ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከነጌሌ አርሲ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ሙግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራች የጨረታው ሰነድ ላይ የተፈረመበት እና የድርጅቱ ማህተም የተደረገበት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ከ07/12/2012ዓ.ም እስከ 27/12/2012ዓ.ም ለ15ታከታተይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ገቢ የሚሆነው እና የሚከፈተው ነጌሌ አርሲ ከተማ አስ/ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት በ28/12/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ያሸነፈውን ዕቃ እስከ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0468106669 ፣0913219740 ፣ 0919686209 ደውሎ መረዳት ይቻላል ፡፡
የነጌሴ ኣርሲ ከተማ ኣስ/ገ/ኢ/ ትብብር/ጽ/ቤት