ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቻግኒ ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ ለ2013 በጀት አመት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የደንብ ልብስ
- ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 ህትመት
- ሎት 4 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 5 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 6 የተለያዩ መሳሪያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሳተም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ያላቸው ከ200,000 ብር በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ሰነዶች ኮፒ ተደርገው ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማያያዝ የሚችሉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ቦታ ቻ/ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ ግዥ እና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 ነው፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨራታውን ሰነድ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት እስከ 15ኛው ቀን 4፡00 ጤና ጣቢያ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ 50 ብር በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ማንኛውም ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በጤና ጣቢያው ግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ15ኛው ቀን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨርሰው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨራታ ማስተወቂያው 16ኘው ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡15 ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን ቢገኙም ባይገኙም በግልፅ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት ስለሆነ የሙሉ እቃ ዋጋ መሙላት አለበት፡፡ ካልተሞላ ግን ከጨረታ ውጭ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅት እቃዎችን ጤና ጣቢያ የንብረት መጋዝን ድረስ በማቅረብ ጥራታቸውን ታይቶ በዝርዝር ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሽናፊ እቃውን ማቅረብ ያለበት የጨረታ ሰነዱ ላይ የተሠጠውን ዝርዝር እቃ እንጅ ስርዝ ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው የዋጋ መሙያ ፎርም በስተቀር በማሳሰቢያ የሚሞሉ ዋጋ እና ሞዴል መረጃን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በአካል መገኘት ወይም በስልክ 0582251960 ወይም 0582250002 በመደወል ማግኘት ትችላለችሁ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ውል ሲወስድ ናሙና የሚያስፈልግ ከሆነ ማቅረብ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ቻግኒ ከ/አስ/ጤ/አጠ/ጣቢያ