የጨረታ ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በታች የተገለፀውን እቃና አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የእቃና አገልግሎት ዓይነት |
የጨረታ ቁጥር |
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት
|
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በ ብር СРО |
1 |
Lot upgrading UPT cable to Fiber optic cable |
E/EMIS/ NCB/01/01/2012 |
ግንቦት 19/2012 ዓ,ም ሰዓት 4፡00 ጠዋት
|
ግንቦት 19/2012 ዓ,ም ሰዓት 4፡30 ጠዋት
|
ብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ)
|
- ተጫራቾች የታሸገ የመጫረቻ ሰነድ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሲሆን ሥርዓቱም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳዳር አዋጅና መመሪያ መሠረት ነው፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በተራ ቁጥር 7 የተገለጹትን ሰነዶች በመያዝ በአማርኛ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትምህርት ሚንስቴር ሂሳብ ቁጥር 1000003784828 ገቢ በማድረግ ፋይናንስ አስተዳዳር ቢሮ ቁጥር 09 ገቢ ያደረጋችሁበትን በማሳየት ደረሰኝ በመያዝ ከቢሮ ቁጥ 21 ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው የት/ሚኒስቴር አራት ኪሎ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 21 ነው
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሠንጠረዥ የተገለፀው የገንዘብ መጠን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳዳሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው ጨረታ ሰነድ ምእራፍ 1 ክፍል 4 የተመለከቱትን ሠነዶች/ቅፆች/ በመሙላት ይሆናል፡፡ ዝርዝር ፍላጎት መግለጫውን ከጨረታ ሠነዱ ጋር ተያይዞ ቀርቧል፡፡
- ተጫራቾች የሚከተሉትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም በዘርፉ
- የግብር ግዴታ ለመወጣት ከሀገር ውስጥ ገቢ ወይም ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሑፍ ማስረጃ
- የተ.እ.ታክስ/ቫት/ ሠርተፍኬት
- የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዌብ ሳይት ላይ የተመዘገበ
- የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅጽ ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት
8. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011 1 56 55 30/58 መጠየቅ ይችላሉ።
የትምህርት ሚኒስቴር