የጨረታ ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በታች የተገለጹትን የHigh Performance Workstation ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈለጋል::
ተ.ቁ |
የእቃው ዓይነት |
የጨረታ ቁጥር |
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ
|
1 |
High-Performance Workstation |
MOE/NCB/ 01/01/2012
|
ሰኔ 15/2012 4፡00 ሠዓት
|
ሰኔ 15/2012 4፡30 ሠዓት
|
20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/
|
- ተጫራቾች የታሸገ የጨረታ ሰነድ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሲሆን ሥርዓቱም በመንግስትና ግዥ ንብረት አስተዳደር አዋጅና መመሪያ መሠረት ነው::
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በተራቁጥር 7 የተገለጹትን ሰነዶች በመያዝ በአማርኛ የተዘጋጁ የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000003784828 ገቢ በማድረግ ፋይናንስ አስተዳዳር ቢሮ አሮጌው ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ገቢ ያደረጋችሁበትን በማሳየት ደረሰኝ በመያዝ ከቢሮ ቁጥር 10 ሰነድ መውሰድ ይችላሉ::
- ጨረታው የሚከፈተው የት/ሚኒስቴር አራት ኪሎ ዋና መስሪያ ቤት ግዥ አገልግሎትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር አሮጌው ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ ነው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሠንጠረዥ የተገለፀው የገንዘብ መጠን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው ጨረታ ሰነድ ምእራፍ 1 ክፍል 4 የተመለከቱትን ሠነዶች/ቅፆች በመሙላት ይሆናል:: ዝርዝር ፍላጐት መግለጫውን ከጨረታ ሠነዱ ጋር ተያይዞ ቀርቧል፡፡
- ተጫራቾች የሚከተሉትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው። ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ:: በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም በዘርፉ የግብር ግዴታ ለመወጣት ከሀገር ውስጥ ገቢ ወይም ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሑፍ ማስረጃ –የተ.እ.ታክስ/ቫት ሠርተፍኬት የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዌብ ሳይት ላይ የተመዘገበ
- የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅጽ ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም የተደረገበት
- መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-TeL:0118722896 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር