የጨረታ ማስታወቂያ
ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ በታች የተገለፁትን የተሽከርካሪ ጥገና ለአንድ ዓመት ኮንትራት እንዲሁም የሆቴል ግዥ በአዲስ አበባ ከተማ ለአንድ ዓመት ኮንትራት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ቁጥር |
ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት |
ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ
|
ምርመራ |
1 |
የተሽከርካሪ ጥገና
|
MoE/ NCB/25/2013/ |
ኅዳር 29/2013ሰዓት 4፡00 ጠዋት
|
ኅዳር 29/2013ሰዓት 4፡30 ጠዋት
|
250,000.00 (ሁለት መቶሃምሳ ሺህ ብር)
|
ለአንድ ዓመት ኮንትራት
|
2 |
የሆቴል ግዥ በአዲስ አበባ ከተማ
|
MoE/ NCB/01/24/2013 |
ኅዳር 30/2013ሰዓት 4፡00 ጠዋት
|
ኅዳር 30/2013ሰዓት 4፡30 ጠዋት
|
30,000.00 ( ሰላሳ ሺህ ብር)
|
ለአንድ ዓመት ኮንትራት
|
- ተጫራቾች የታሸገ የጨረታ ሰነድ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሲሆን ሥርዓቱም በመንግሥትና ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅና መመሪያ መሠረት ነው፡፡
- ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች በተራ ቁጥር 7 የተገለጹትን ሰነዶች በመያዝ በአማርኛ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 50/ሃምሣ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ 1000003784828 ገቢ በማድረግ ፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ እሮጌው ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ገቢ ያደረጋችሁበትን በማሳየት ደረሰኝ በመያዝ ከግዥ አገልግሎትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ አሮጌው ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው የት/ሚኒስቴር አራት ኪሎ ዋና መስሪያ ቤት ግዥ አገልግሎትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ አሮጌው ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሠንጠረዥ የተገለፀው የገንዘብ መጠን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው ጨረታ ሰነድ ምዕራፍ 1 ክፍል 4 የተመለከቱትንሠነዶች/ቅፆች/በመሙላት ይሆናል፡፡ ዝርዝር ፍላጐት መግለጫውን ከጨረታ ሠነዱ ጋር ተያይዞ ቀርቧል፡፡
- ተጫራቾች የሚከተሉትን ማስረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ይህን ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭሊሆኑ ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም በዘርፉ
- የግብር ግዴታ ለመወጣት ከሀገር ውስጥ ገቢ ወይም ከሚመለከታቸው አካላት
- የተሰጠ የጽሑፍ ማስረጃ
- የተእታክሰ/ቫት/ ሠርተፍኬት
- የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዌብ ሳይት ላይ የተመዘገበ
ትምህርት ሚኒስቴር