የጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ብርሃን ሕፃናትና ቤተሰብ ልማት ድርጅት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ የማኅበረሰብ አባላት ድጋፍ የሚውል አንደኛ ደረጃ የስንዴ ዳቦ ዱቄት ከአምራች ፋብሪካዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በመሆኑም በዘመኑ የታደሰ ፍቃድ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ እና የቲን መለያ ቁጥር ያላችሁ ተጫራቾች የትራንስፖርት እና የጉልበት ዋጋን ጨምሮ አንድ ኩንታል አንደኛ ደረጃ የስንዴ ዳቦ ዱቄት የምታቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በባሶና ወራና ወረዳ ቀይት ቀበሌ በሚገኘው በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት እንድትወዳደሩ እየጋበዝን፤ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ተዘግቶ በ4፡30 የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን::
ድርጅቱ
ማሳሰቢያ፡-
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታው የሚከፈተው መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ቀይት (ከደ/ብርሃን ከተማ ወደ ደሴ መንገድ 16 ኪ/ሜ ርቀት ላይ) ነው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::አሸናፊ ተጫራቾች የግዢ ማዘጋ በደረሳቸው በ15 ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው ይህ ካልሆነ ግን ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ አይደረግላቸውም::