የጨረታ ማስታወቂያ
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩ የተለያዩ ዕቃዎችንና አገልግሎቶች፡
- ሎት 01 የማገዶ እንጨት ግዥ፣
- ሎት 02 – የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ ፣
- ሎት 03- የመጋረጃ እና ምንጣፍ ግዝ
- ሎት 04 መኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ፣
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 79ኛ ዓመት ቁጥር 189 ቀን መጋቢት 9/2012 ዓ.ም ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ የሚታወቅ ሲሆን በሀገራችን በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ-19/ ስርጭት ምክንያት ጨረታው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘመ የሚታወቅ ሲሆን አሁን መንግስት የሚሰጠውን ጥንቃቄዎች እየተደረገ ጨረታውን ለማስካሄድ ስለተፈለገ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 (አምስት) ቀናት ቆይቶ በስድስተኛው ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በአዲስ አበባ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስ/ማስ/ጽ/ቤት እና ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አስ/ር ህንፃ 2ተኛ ፎቅ ሴኔት አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ስለሚከፈት፤
- በሎት 01-የማገዶ እንጨት ግዥ እና ሎት 03- የመጋረጃ እና ምንጣፍ ግዥ ጨረታ ሙሉ በሙሉ የተሰረዘ ስለሆነ በዚህ ሎት ለመወዳደር የጨረታ ሰነድ የገዛችሁ ድርጅቶች በሌላ ጊዜ ጨረታ ሲወጣ እንድትወዳደሩ፣
- በሎት 02-የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ እና ሎት 04-መኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ የጨረታ ሰነድ የገዛችሁ ድርጅቶች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የጨረታ ሰነድ በማስገባት እንድትወዳደሩ፣
- በሎት 02-የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ እና ሎት 04-መኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ የጨረታ ሰነድ ያልገዛችሁ ድርጅቶች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ በመግዛት እንድትወዳደሩ፣
- የጨረታውን መስፈርትና ዝርዝር ሃሳቦችን ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ 79ኛ ዓመት ቁጥር 189 ቀን መጋቢት 9/2012 ዓ.ም ከወጣው ማስታወቂያ ማግኘት ትችላላችሁ፣
- በጨረታ አከፋፈት ሂደት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉልም፣
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፣
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብት አለው፣
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡– 047 452 45 88 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ