የሀገር ውስጥ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የ/የግ/ማህበር
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ልዩ ልዩ የሕትመት ማሽነሪ መለዋወጫዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር መለያ ቁጥር፣ የቫትተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና የንግድ ሰርተፊኬት እና ሌሎች የህጋዊነት ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ / ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከግዥ ንብረት ከምችት ክፍል በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሁለተኛው ማስታወቂያ ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች ፖስታዎቹን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ በድርጅቱ የግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- የጨረታው ሰነድ ፋይናንሽያልና ቴክኒካል በተለያየ ፖስታ መቅረብ ያለበት ሲሆን የእነዚህም ሰነዶች ኦሪጅናልና ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ መቅረብ አለበት።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ባለው የስራ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል ፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ስልክ ቁጥር 011 551 24 66 / 011 515 50 05
ፋክስ 011 551 86 96
ፖሣ.ቁጥር… 2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ