የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን አቧሬ ለሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን የደህንነት ካሜራ አቅርቦትና የመትከል ስራ የአገልግሎት ግዥ በአስቸኳይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በሚፈለገው የስራ ዘርፍ ተዛማጅ የስራ ልምድ ያላቸውን፤ ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች/አገልግሎት ለመስጠት/ምዝገበና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ (ቢጋር (TOR)) 1ኛ ፎቅ ድርጅቱ አዲሱ ህንጻ በሚገኘው ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ከዕለት ገንዘብ ተቀባይ
የማይመለስ ብር 100.00 ከፍለው በመግዛት የጨረታ ሰነዱን በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በአቅርቦትና ሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች የፋይናንሻይልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ሐምሌ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ ብቻ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በአቅርቦትና ሎጀስቲክስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ስልክ ቁጥር 011-1-564910/011-1553233
የውስጥ መስመር 348
ፋክስ ቁጥር 251-11-1-553939
አዲስ አበባ
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት