የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- በጨረታ አንድ (ሎት 1)፡– ቋሚ የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ /ሀይድራንት ሲስተም ዝርጋታ አገልግሎት ግዥ፣
- በጨረታ ሁለት (ሎት2)፡– የተለያዩ ያገለገሉ ማሽኖች ግዥ ማለትም perfect binding machine 2 unit offset printing press (GTO) machine folding machine hot foil stamping machiner one knife paper cutter machine letter press platen(21X30) machine
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው፣ በሚፈለገው የሥራ ዘርፍ ተዛማጅ የስራ ልምድ ያላቸውን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 1ኛ ፎቅ የድርጅቱ አዲስ ህንፃ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 100.00 ከፍለው በመግዛት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ አሮጌው ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቶች የፋይናንሽያልና የቴከኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኢንቨሎኘ በማድረግ ማቅረብና ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋቸው 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ከፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
ጨረታው በ24/2/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፣ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሽያል የመጫረታ ሠነዶች የሚከፈቱት ቴክኒካል ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው:: ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ስልክ ቁጥር 011-1-564910/011-1553233 የውስጥ መስመር 348
ፋክስ ቁጥር 251-11-1553939
ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት