የጨረታ ማስታወቂያ
ማህበራችን ብራይት ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 1- ሀ የደ/ጭ/ማመ/ባለ ማህበር ያገለገለ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
በመሆኑም ተሽከርካረውን ለመግዛት የምትፈልጉ በሥራ ሰዓት ለቡ መብራት ሀይል ወደ ጀሞ በሚወስደው መንገድ ዘመን ማደያ ጎን ካሌብ ህንፃ (አባይ ባንክ ያለበት ህንፃ) 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን እየመጣችሁ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ 6፡30 ድረስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን::
- ጨረታው ጥቅምት 13 2013 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴታ ታክስን ያካተተ መሆን አለበት
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ 50,000.00 (ሃምሳ ሺ) ብር በCPO በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- በጨረታው ለተሸነፈ ተጫራች ያስያዙት C.P.O ወዲያው ይመለስላቸዋል::
- አሸናፊው ከጨረታው በኋላ ያለውን የተሽከርካሪ ስም ማዞሪያና ሌሎች ወጭዎች በሙሉ ይሸፍናል::
- አሸናፊው ንብረቱን ጨረታው ከተካሄደበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን በመፈፀም እንዲረከብ ይገደዳል::
- ተሽከርካሪውን በተባለው ቀን ውስጥ ተረክቦ ካልወሰደ ለጨረታ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግም
- ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 0912-697475/0929-907021
የቢሮ ስልክ 011-8-495875