የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2012
ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ ለህትመት አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የመዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቶች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ 700 ሜትር አካባቢ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜን 6 ሰዓት ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 32 መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቶች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሙግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ኛው የሥራ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 በመቅረብ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያቸውን ማስገባት ይችላሉ፣
- ማንኛውም ተጫራች የዕቃውን የማስረከቢያ ጊዜ መጠቀስ አለበት፣
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዋናው መ/ቤት በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ድርጅቱ መጋዘን ድረስ ለማቅረብ ያካተተ መሆን አለበት፣
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
- ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ 700 ሜትር ላይ ስልክ ቁጥር 011-4-4264-80 ፖሢቁ22457 አዲስ አበባ
የብራና ማተሚያ ድርጅት