የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 09/2012
ብራና ማተሚያ ድርጅት የተለያዩ ለህትመት አገልግሎት የሚውሉ ጥሬ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት የሀገር ውስጥ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪእሴት ታክስ ከፋይነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ 700 ሜትር አካባቢ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 32 መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 በመቅረብ ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የዋጋ ማቅረቢያቸውን ማስገባት ይችላሉ፤
- ማንኛውም ተጫራቾች የዕቃውን የማስረከቢያ ጊዜ መጥቀስ አለበት፤
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በዋናው መ/ቤት በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ድርጅቱ መጋዘን ድረስ ለማቅረብ ያካተተ መሆን አለበት፤
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፡-
ብራና ማተሚያ ድርጅት
ከወሎ ሰፈር ወደ ጎተራ 700 ሜትር ላይ
ስ.ቁ. 011-4-4264-80
ፖ.ሳ.ቁ.22457
አዲስ አበባ
የብራና ማተሚያ ድርጅት