የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02 2008
ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመፃህፍት ኤጀንሲ የተለያዩ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ማለትም
- ሎት፤1 ፈርኒቸር
- ሎት2፤ የኤሌክትሮኒክስና የአይቲ ዕቃዎች
- ሎት 3፤ የመኪና ሰርቪስና ጥገና
- ሎት፤4 ግማሽ ሊትር ውሃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡–
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሥፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ በየሥራ ዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ ፣ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃዎቻቸውን ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታውን መካፈል የሚፈልጉ ሁሉ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኤጀንሲው ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 110 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም ለኤጀንሲው ገንዘብ ቤት በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ሲፒኦውን ወይም ደረሰኛቸውን ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በተለየ ፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ግዥ ክፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኤጀንሲው የግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 110 ይከፈታል፡፡ ሆኖም 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ኤጀንሲው ለግዥው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ሬዲዮ ፋና ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡– 011 515 92 37/011 550 80 30
ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመፃህፍት ኤጀንሲ