የጨረታ ማስታወቂያ
የብሄረ ኢትዮጵያ አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ብሄረ ኢትዮጵያ አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ለአገልግሎት የሚውሉ
- የደንብ ልብስ ስፌት የደንብ ልብስ ፣
- የትምህርት ዕቃዎች፣
- ህትመት ፣
- የህክምና ዕቃዎች ፣
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የላብራቶሪ ዕቃዎች ፣
- የጽዳት ዕቃዎች ፣
- ቋሚ ዕቃዎችና የፕላንት ማሽነሪ ግዥና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል
2.የዘመኑ ግብር የከፈለና ፍቃዱንና ዋናውን በማሳየት ኮፒ ማቅረብ የሚችል
3. የግብር መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፍኬት የሚያቀርብና ቫት ተመዝጋቢ የሆነ
4. ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ በት/ቤቱ ብሄረ ኢትዮጵያ አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ስም 2% ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ለተወዳደረበት ዕቃ ከመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።
5. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይታሽግና 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት በት/ቤቱ በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል
6. ለተዘጋጀው ዝርዝር ጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሚጫረትበት ዕቃ የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላል
7. ሌሎች ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም
8. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው የአንድ ዋጋ ላይ ቫትን /15%/አካቶ ማቅረብ አለበት
9. ተጫራቾች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው
10. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ ዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ታክሲ ማዞሪያ
ስልክ ቁጥር 011 1 26 05 14 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7
ብሄረ ኢትዮጵያ አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት