ጨረታ ማስታወቂያ
ባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት ከቻይልድ ፈንድ ጋር በአጋርነት የሚሠራ መንግሥታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት ሲሆን፤ ከዚህ በታች የተገለፁትን የግንባታ ዕቃዎች እና ፕላስቲክ ወንበሮች ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
ምርመራ |
1 |
የቤት ክዳን ቆርቆሮ 35 ጌጅ |
ከ1000 በላይ |
|
2 |
ሚስማር |
130 ፓኬት በላይ |
የቆርቆሮን ጨምሮ |
3 |
መደገፊያ የሌለው ፕላስቲክ ወንበር |
ከ1000 በላይ |
|
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ቢያንስ የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በሕንፃ መሣሪያ አቅርቦት እና የፕላስቲክ ወንበር አቅርቦት ንግድ ፍቃድ ያለው፤ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድና ምዝገባ ፈቃዳቸውን፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት፣ በጨረታ እንድትሳተ ፤ ለዘመኑ በጀት ዓመት ብቻ የሚያገለግል የምሥክር ወረቀት እና ቲን ሠርተፍኬት ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 6፡30 እና ከ7፡30 -11፡30 ሰዓት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በማያያዝ ዲላ በሚገኘው ባላያ የሕ/ቤ/በ/ቅ/ድርጅት ጽ/ቤት ሂሣብ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሠነድ መግዛት እና የጨረታ ሠነዱን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ (ፖስታ) በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሰባተኛው /7ኛው/ ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ድረስ ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ዲላ በባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጎኙበት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-331-00-49/046-331-31-45 ዘወትር በሥራ ሰዓት ደውሎ መጠየቅና መረዳት ይቻላል፡፡
- አድራሻ፡– ባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት ደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ ጌዲዮ ዞን ዲላ ከተማ ከዲላይት ኢንተርናሽናል ሆቴል 100 ሜትር ገባ ብሎ፡፡
ባላያ የሕፃናትና ቤተሰብ በጎ አድራጎት ድርጅት