የጨረታ ማስታወቂያ
ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- የደንብ ልብስ፣
- አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሌሎች መሣሪያዎች
- የህክምና ዕቃዎች፣
- ቋሚ ዕቃ
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የቫት ከፋይ ሰርተፍኬት ስገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የዕቃና አገልግሎት ግዥ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ የጨረታውን ዋጋ 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከላይ ለተዘረዘሩ ዕቃዎች ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ 100 (መቶ ብር ብቻ )በመክፈል ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አ/ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ በመሙላትና በኤንቨሎፕ በማሸግ ዋናውንና ኮፒውን ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 6 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃ ሁሉ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ሲኖርበት ናሙና ለማያቀርብላቸው ዕቃዎች ዝርዝራቸውን ወይም ስለዕቃው የሚገልጽ ዝርዝር እስፔስፊኬሽን እና ፎቶ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ህዳር /03 /2013 ዓ/ም ከቀኑ 11 ሰአት ይዘጋና በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ሂደት ቅሬታ ያለው አካል ጨረታው ከተከፈተ እስከ 3 ቀን ድረስ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ላሸነፈው ዕቃ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መዋዋል ግዴታ ሲሆን አልዋዋልም ቢል ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት ናሙና መሰረት አሸናፊ ሲሆኑ ያሸነፉበት ዕቃ በናሙናው መሰረት ማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ካላቀረቡ በህግ ይጠየቃሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስቁ፡- 011 442 60/36 32 38 31 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ ፡- ሳሪስ ሬስ ኢንጅነሪንግ ጀርባ
የቡልቡላ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ት/ቤት