የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ፌቴሙ/መ/ጨ/2/ 2013
የፌዴራል ቴክኒከና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ በ2013 ዓ/ም ከመንግስት በተገኘ መደበኛ በጀት የተለያዩ እቃዎችን ማለትም
- የአይሲቲ እቃ ፤
- የጽሕፈት መሳሪያ ፣
- የጽዳት እቃ ፤ ልዩ ልዩ እቃ ፤
- የመኪና እቃ ፤
- የደንብ ልብስ፤
- የእድሳትና ጥገና እቃ ፤
- የህንጻ ቁሳቁስ እቃ ፤
- የፕሪንተር ቶነር ፤
- የጥበቃ አገልግሎት፣
- የጽዳት አገልግሎት ፤
- የህትመት አገልግሎት
- የትራንስፖርት አገልግሎት ::
ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ ፍላጎት ያላችሁ
- በዘርፉ ዕቃና የአቅርቦት አገልግሎት ዝርዝር ላይ የተመዘገባችሁ አና የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት /VAT/ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን/ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማረጋገጫና የሰፕላየር ሊስት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልፅ የመወዳደሪያ ሠነዶቻቸውን ቴክኒካል 1 ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒውን እንደዚሁም ፋይናንሽያል 1 ኦሪጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታውቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን በፈዴራል ቴክኒክ ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጀንሲ ላምበረት መናኸሪያ አጠገብ በሚገኘው ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107 ቀርበው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ልክ ከቀኑ 400 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4.30 ሰዓት ላይ በግልፅ ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ / በዓል ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ይከናወናል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሠነድ የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ፌደራል ቴከኒከና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኤጄንሲ 1ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 107 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን 10% እንደሁኔታው ከዛም በላይ በማስያዝ ባሸነፉበት በ7ኛ ቀን ውስጥ ውል ሳይገባ ለጨረታ ያስያዘው ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ ጨረታው 2ኛ ለወጣው ወይም ይሰረዛል ፡
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ–ሥርዓት ባይገኙ የጨረታውን ሂደት እያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም ለተዘረዘሩ እቃዎችና አገልግሎቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ ተጠቅሷል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፤0118619764 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ
የግዢና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ/