ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማረሚያ ቤት ለህግ ታራሚዎች አገልግሎት የሚውል የበሰለ ምግብ አቅርቦት ሐምሌ 1 /2012 –ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ለአምስት ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ማንኛውም በጨረታ ለመካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ፡
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ቢሮ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበና በ2012 ዓም የሥራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እና አግባብነት ያለው የንግድና ሥራ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ የተመዘገቡ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ፣
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 30.00 (ሠላሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እትም ከወጡበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማረሚያ ቤት ከሚገኘው ሰበታ ከተማ በተለምዶ ዳላቲ የሚባለው ስፍራ ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በዞኑ ማ/ቤት አስ/ጽ/ቤት ለዚሁ የተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ከመቶ 2 በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (CPO) እና የምግብ እህል ናሙና ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተደራጅቶ የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀን በተከታታይ በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት በማ/ቤት አስ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚዎች ኮሚቴዎች የመ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉ እቃዎችን በራሳቸው መጓጓዣ ማረሚያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማረሚያ ቤት ውስጥ በተዘጋጀው ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ ማቅረብ የሚችል፡፡
ማሳሰቢያ፡ለተለያዩ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011 829 08 687 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማረሚያ ቤት