የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡ ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆ/ግ/ን/አስ/ማስ/03/02/2013 በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህ.ጤ.ሳኮ እና አጢ/ስፔ/ሆስፒታል በ2013 በጀት ዓመት ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ:-
- የተለያዩ ህትመቶች ግዥ
በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሰራ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ፡-
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ፥ የተጨማሪ እሴታ(VAT) ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርቲፊኬት ያላቸው፣ በ2013 ዓ/ም በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና ስግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ድህረ ገጽ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ኣየር ላይ ከዋለበትቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ጎ/ዩኒ/ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስ ፋይናንስና በጀት ዋና ገንዘብ ቤት መግዛት ይቻላል፤
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት የገንዘብ መጠን ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ከ118 ቀን ያላነስ በሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ወደ ጨረታ ሳጥን የሚገቡ ሰነዶች፡– ሀ/ ተ/ቁ 1 የተጠቀሱትን ቴከኒካል ሰነዶች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ኮፒ፤ የጨረታ ማስከበሪያ፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የገቡበትን ኦርጅናል ቅፅ ሞልተው ፈርመውና በድርጅቱ ማህተም አረጋግጠው፣ በኣንድ ፖስታ፤ ለ/ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ኦርጅናል በአንድ ፖስታ፣ ሐ/ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ኮፒ ስኣንድ ፖስታ በማሸግና ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናትና በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በስራ ሰዓት ጎንደር ዩኒቨርስቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 26 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን፣ የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎን/ዩኒ/ህ/ጤ/ሳ/ኮ/እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ሳይገኝ ሲቀር የጨረታዉን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡የመክፈቻዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- የሚሞላው ዋጋ ዕቃዉን ጎዩ/ ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ለማቅረብ የማጓጓዣ፣ የጉልበት ዋጋና ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፤ የታከስ ሁኔታ ያልተገለፀ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጭን አካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎችን ማሰረከብ የሚችለው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ እና አጠ/ስፔ/ሆ ግቢ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ እስከ 90 ቀን ድረስ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የዕቃውን ብዛት 20% ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ፣ ውሉ ከተጠናቀቀም በኋላ እስከ 25% ተጨማሪ ውል የመውሰድና የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስ/ቁጥር፡– 0582115186 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ
የህ.ጤ.ሳ.ኮ.እና ወ/ስፔ/ሆስፒታል