የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህ.ጤ.ሳ.ኮ.እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል በ2013 በጀት ዓመት ለተለያዩ የሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ፤
- ሎት-1- የኦክስጅን ጋዝ፣
- ሎት-2- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት-3- ቋሚ አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ግዥ
በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ አውጥተው ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት (VAT) ተመዝጋቢ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርቲፊኬት ያላቸው፣ ከምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን የተሰጠ የዘመኑ የብቃት ማረጋገጫና በ2013 ዓ.ም በጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ እና በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ድረ–ገጽ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ጎ/ዩኒ/ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስ ፋይናንስና በጀት ዋና ገንዘብ ቤት ወይም አዲስ አበባ ከዛንችስ ኢንተር ኮንቲኔታል (ኢንተር ቢስትሮ ካፌ) ፊት ለፊት ከሚገኘው ጎን/ዩኒ/ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል፤
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት የገንዘብ መጠን ለሎት-1- ብር 65,000.00 /ስልሳ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት-2 ብር 55,000.00 /ሀምሳ አምስት ሺህ ብር/ ለሎት-3- ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ከ118 ቀን ያላነሰ በሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ወደ ጨረታ ሳጥን የሚገቡ ሰነዶች፡– ሀ/ ተ/ቁ1 የተጠቀሱትን ቴክኒካል ሰነዶች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ኮፒ፤ የጨረታ ማስከበሪያ፣ የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የገቡበትን ኦርጅናል ቅፅ ሞልተው ፈርመውና በድርጅቱ ማህተም አረጋግጠው፣ በአንድ ፖስታ፤ ለ/ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ኦርጅናል በአንድ ፖስታ፣ሐ/ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ ኮፒ በአንድ ፖስታ በማሸግና ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ሎት -1 እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ፣ ሎት-2- እና ሎት 3- 17ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በስራ ሰዓት ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ/ እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 26 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን፣ ሎት-1- የኦክስጅን ጋዝ በ16ኛው ቀን 4፡00 ስዓት ታሽጎ 4፡30 ሰአት ሎት-2-እና ሎት-3- የጽዳት ዕቃዎች በ17ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎን/ዩኒ/ህ/ጤ/ሳ/ኮ/እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ግዥና ንብረት አስተዳደር ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡ የመክፈቻዉ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል። ለሎት-2-እና ለሎት3- ሳምፕል ለሚጠይቁ ዕቃዎች በመክፈቻው ቀን ርክክብ ይደረጋል፡፡
- የሚሞላው ዋጋ ዕቃውን ጎ/ዩ/ ህጤሳኮ እና አጠ/ስፔ/ሆስፒታል ለማቅረብ የማጓጓዣ፤ የጉልበት ዋጋና ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፤ የታክስ ሁኔታ ያልተገለፀ ከሆነ የተሞላው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጭን አካትቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ዕቃዎችን ማስረከብ የሚችለው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህ/ጤ/ሳ/ኮ እና አጠ/ስፔ/ሆ ግቢ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ እስከ 90 ቀን ድረስ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የዕቃውን ብዛት 20% ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ፣ ውሉ ከተጠናቀቀም በኋላ እስከ 25% ተጨማሪ ውል የመውሰድና የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስ.ቁጥር፡– 0582115186 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፤
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ