የጨረታ ማስታወቂያ
በጋሞ ዞን የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤቶች በ2013 ዓ.ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ማቴሪያሎዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉት :
- የጀነሬተር አይነቶች
- የህንፃ መሣሪያዎች
- የጽሕፈት መሣሪያዎችና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- የሞተር ሳይክል አይነቶች
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
ስለሆነም በመንግሥት ግዥ አዋጅና ደንብ መመሪያ መሠረት፡
- የታደስ የንግድ ፍቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ።
- የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር (Tin Number)።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ መረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ከሽያጭ ዋጋ ላይ የመንግስት ግብር 2% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ።
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት።
- የአቅራብነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታው ሁነታ በአይተም /በጥቅል ሊሆን ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት በእንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በሠ/በር/ሕ/አ/ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፊ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላው ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት።
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት በሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናል።
- በጨረታ ለመሳተፍ በቅድሚያ በተዘረዘረው መሰረት የጨረታ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ በCPO ወይም ባንክ ጋራንቲ እና በጥሬ ገንዘብ 4000 /አራት ሺህ ብር/ ከጠቅላላ ዋጋ በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው የጨረታው ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው በ15ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይሆናል።
- በጨረታ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ድረስ የጫይኚ፣ የአውራጅና የጭነት ወጪን በመሸፈን ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ወይም የተጨራቹ ወኪል ባለመገኘት የጨረታውን መከፈትን አያስተጓጓልም።
- 16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሞባይል ቁጥር 09 10 43 89 07
የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት