የጨረታ ማስታወቂያ
በጉራጌ ዞን የእኖር ኤነር ወረዳ ሚቄ ከተማ የፍርድ ቤት ቢሮ ግንባታ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራች በማመልከቻ ሲጠይቁ፡
- ደረጃቸው ቢሲ/ጂሲ -5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውጽ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሎ።
- የዘመኑን የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚዙት የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዩች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች አሟልተው ሰነድ መግዛት ሲቀርቡ ከጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኮንስትራክሽን ዘርፍ ደብዳቤ ማቅረብ አስባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 6:00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመከፈል ከእኖር ኤነር ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ
- ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፓስታ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000/ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦርጅናል ዶክመንት ጋር በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት/
- ለ/ ለፋይናንሺያል ዶከመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሸግ /ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፓስታ ውስጥ በማሸግ/ፋይናንሺያል በሚል በመለየት እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አስባቸው፡
8. የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በእኖር ኤነር ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ ቤት ስም መሠራት አለበት ::
9. ከተራ ቁጥር 6-8 የተጠቀሱት መስፈርቶች ሙሉ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል።
10. የጨታው ቴክኒካል ዶክመንት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
11. የፋይናንሺያል /የፕሮጀክቱ ግንባታ ዋጋ ከቴክኒክ ግምገማ ውጤት በኋላ የቴክኒከ ግምገማውን ያለፋት ተጫራቾች ሰነድ ብቻ የጨረታው ኮሚቴው በማስታወቂያ በሚገልፀው ቀን ይከፈታል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሣሰቢያ፡-
- በአፈፃፀማቸው ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል።
- በዞናችን ውስጥ ከሁለት በላይ ፕሮጀከት ያላቸው መወዳደር አይችሉም::
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0911788101 ወይም 0937276369
የእኖር ኤነር ወረዳ
ፋ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት
ሚቄ