የጨረታ ማስታወቂያ
05/2012
በጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋ/ኢ/ል ፅ/ቤት ለተለያዩ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የሞተር ሳይክል ግዢ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- የዘመኑ ግብር የከፈለ፣የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- ቲን–ነምበር ያለውና ቫት /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣
- ጨረታው የሚቆየው ከ07/09/2012 ዓ.ም እስከ 21/09/2012 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ሶ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 6 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ21-09/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ 4፡30 ሰዓት ሶ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት የግ/ክ/ን/አስ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁ/ር 6 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ፤ ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና(CPO) ለሞተር ሳይክል ግዢ ብር 5000/ አምስት ሺህ ብር/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊ ድርጅት አሸናፊው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል።
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ሶዶ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል።
- አሸናፊው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ሲፈጽም በግዥ መመሪያው መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- አሸናፊ የሆነው ድርጅት ያሸነፋቸው እቃዎች እስከ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል ።
- ተጫራቾች የስራው ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0468830128 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል።
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት