የጨረታ ማስታወቂያ 01/2013
በጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ለተለያዩ መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያ እቃዎች/በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈለ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- ቲን-ነምበር ያለውና ቫትVAT/ ትመዝጋቢ የሆነ፣
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፣
- ጨረታው የሚቆየው ከ 12/1/2013 ዓ.ም እስከ 26/1/2013 ዓ.ም ሲሆን ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ሶ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁ/ር 6 በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 26/1/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ሶ/ወ/ፋ/ል/ጽ/ቤት የግ/ከ/ን/አስ/ሥ/ሂደት ቢሮ ቁ/ር 6 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ ዋስትና(CPO) ብር 15000/አስራ አምስት ሺህ/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያው ለተሸናፊ ድርጅት አሸናፊው ውል መግባቱ ከተረጋገጠ በኋላ ይመለስለታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱን ከተረጋገጠ እስከ ሶዶ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት በመቅረብ ውል መፈጸም ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ሲፈጽም በግዥ መመሪያው መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች እስከ ሶዶ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- .ተጫራቾች የስራው ዝርዝር የያዘ ሰነድ ሶዶ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ ብር 100/አንድ መቶብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0468830533/128 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት