የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መለያ ቁጥር CCA–Branch-01/2013
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በ 2013 በጀት ዓመት ለቅ/ጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ግዥ አወዳድሮ ቋሚና አላቂ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ፣
- የደንብ ልብስና አልባሳት ፤ ጫማ
- አላቂ የቢሮ መገልገያ እና የፅዳት እቃዎች
- የተሸከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ጎማዎች፣ ዘይትና ቅባት፣
- የኤሌክትሪክ እና የሕንፃ መሣሪያዎች
- ቋሚ የቢሮ እና የቤት እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም እቃዎችን የሚያመለክተው የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጨረታ ሠነዱ ላይ መመልከት ትችላላችሁ፡፡
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለ ስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ ሲኤሚሲ/ሚካኤል ቤ/ክ ፊት ለፊት ዴሉክስ ፈርኒቸር ሕንፃ ጀርባ ከሚገኘው ፀዳ ሕንፃ የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት የግዥ ቡድን ሕንፃ ሦስተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ ፣
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፤
- ጨረታው ከ8/3/2013 እስከ 22/3/2013 ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀን በአየር ላይ የሚቆይ መሆኑ ይታወቅ
- ጨረታው ህዳር 23/3/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፣
- የጨረታው አሸናፊ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ ) CPO በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፤
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያለፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የጉምሩከ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት ሲኤምሲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፤
- ጨረታውን የምናስተናግደው በጠቅላላ ድምር/በሎት/ድምር ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም፤ ካለውም ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸው ማህተም እንዲሁም ስም፣ አድራሻ፣ስልክ፣ ኢሜይል አድራሻ ማድረግ አለባችሁ፡፡
- መ/ቤቱ የሚገዛውን እቃ በአሸናፊው ተጫራች ያቀረበው በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት በጥቅል ድምር ስለሆነ የእያንዳንዱ እቃ ዋጋ ዝርዝር መሞላት አለበት፡፡ ካልተሟላ ግን ከጨረታው ውጪ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ተመሳሳይ ዋጋ ቢያቀርቡ ቃለ ጉባኤ በመያዝ በዕጣ የምንለይ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ዘግይቶ የመጣ ተጫራች ፖስታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር ፦ 022 224-02-47/022-224-16-88/
09-42-30-88-99 /09-21-41-52-20/ 09-28-2407/09-18-08-97-37
የጉምሩክ ኮሚሽን አዋሽ ቅ/ጽ/ቤት