የጨረታ ማስታወቂያ /ቁጥር 001/01/13
በጉለሌ ክ/ከ በወረዳ 8 አስተዳደር ብርሀነ ህሊና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተገለጹትን ግዥዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1- ስቴሽነሪ ዕቃዎች፣
- ሎት 2 – የደንብ ልብስ፣
- ሎት 3- የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 4- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ሎት 5- ኤሌክትሮኒክስ እና የተለያዩ ዕቃዎች
በመሆኑም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ
- አንዱ በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም::
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1- 1000.00 ለሎት 2- 2000.00 ለሎት 3 -1000.00 ለሎት 4 -000.00 ለሎት 5-1000.00 በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባችሁ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ድረስ ከት/ቤቱ ግዥ ክፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናሉን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 9፡30 ሰዓት ድረስ በጉለሌ ክ/ከ በወረዳ 8 አስተዳደር ብርሀነ ህሊና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ10ኛው ቀን በ9፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10:30 ላይ በርዕሰ መምህር ክፍል ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ የማድረስ ግዴታ አለባቸው፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 154 62 25 / 0111 27 07 55 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡-ጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 8 ከአዲሱ ገበያ ወደ ቶታል በሚወስደው መንገድ ጎጃም በር አደባባይ ሳይደርሱ መርሀቤቴ ሆቴል አጠገብ ወደ ሩፋኤል በሚወስደው አስፓልት መንገድ ትንሽ ገባ እንዳሉ ያገኙታል፡፡
በጉለሌ ክ/ከ በወረዳ 8 አስተዳደር
ብርሀነ ህሊና የመጀመሪያ
ደረጃ ት/ቤት