የጨረታ ቁጥር 001
የግልጽ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የአስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ ቤት የግዥ ቡድን የ2012 በጀት ዓመት የእቅድ ማስፈፀሚያ የሚውሉ የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት 2 የመስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት 3 የውሃ አቅርቦት አገልግሎት
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
- በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ስርተፍኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው ፣
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1 6ooooo ብር ፣ሎት-2 10.000.00 ብር ፣ ሎት-3 -10,000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር ጉዳዮችና የተጫራቾችን መመሪያ የያዘ ሰነድ ጨረታውጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 100.00/መቶ ብር/ በመግዛት 9ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ፣
- ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጉ ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል ፣ ህጋዊ ወኪል ለመሆናችሁ የሚገልጽ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውሉን በተፈራረመበት በ15 ቀን አገልግሎት መስጠት አለበት፣
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው እና በእያንዳንዱ ላይ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማህተም ያላደረጉ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ ይሆናሉ፣
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሞሉትን ዋጋ /VAT/ ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጥቀስ ይኖርበታል፡፡ ካልተጠቀሰ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፣
- ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ለየብቻ አድርጎ በማያያዝ ማስገባት ይኖርበታል፣
- በጨረታው ላይ 20% መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል፡፡
- በውሉ ላይ 25% መጨመር ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ አዲሱ ገበያ ኖክ
ጀርባ የጉ/ክ/ከተማ አዲሱ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ በስልክ ቁጥር፡– 0118279528 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉለሌ ክ/ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት