የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
01/2013
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2013 በጀት አመት የተለያዩ እቃዎችን
- ሎት 1 የህክምና እቃና መድሀኒቶች ፣
- ሎት 2 ቋሚ እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 4 የጽህፈት መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ፣
- ሎት 5 የደንብ ልብሶች እና የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት 6 የህትመት ውጤቶች ፣
- ሎት 7 የህንፃ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ዕድሳት እና ጥገና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ፡–በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በየዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No ) ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ከ50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (Vat ) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት እቃ
- ሎት 1- 9000 /ዘጠኝ ሺ ብር ብቻ/
- ሎት 2 6,000/ስድስት ሺ ብር ብቻ/
- ሎት 3- 4500/አራት ሺ አምስት መቶ ብር ብቻ/
- ሎት 4- 3000 /ሶስት ሺ ብር ብቻ/
- ሎት 5 -4500/ አራት ሺ አምስት መቶ ብር ብቻ/
- ሎት 6 -4700 /አራት ሺ ሰባት መቶ ብር ብቻ፣
- ሎት 7- 3000 /ሶስት ሺ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚገባቸው ሲሆን ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ውስጥ ያስረክባል።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 ( አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 42 ፊት ለፊት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 42 ፊት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ጨምሮ ዋጋ ሞልቶ፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ አድርጎ የማይቀርብ ተጫራቾች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል ::
- የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው(በአስረኛው) ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘጋጅቶ በዛው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ( ህጋዊ ወኪል ) በተገኙበት ወይም ባይገኝም በግልፅ ይከፈታል ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ናሙናውን በመስሪያ ቤቱ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 42 በሚገኘው የግዥ ቢሮ ገቢ ማድረግ አለባቸው:: ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል። ቋሚ ዕቃዎችን በተመለከተ ደረጃቸውን የሚገልጽ እስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: የህንፃ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ዕድሳት እና ጥገና በተመለከተ በጥቃቅንና አነስተኛታዳጊ ከዚያ በላይ በኮንስትራክሽን የተደራጁ ለስራው ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው::
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
- መ/ቤቱ ጨረታውን 20% ጨምሮ ወይም 20% ቀንሶ መግዛት ይችላል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011154 6029/0111 2680 48/47 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ፡– ጉለሌ ክ/ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ጃምቦ ህንጻ ፊት ለፊት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጉለሌ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት
የአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ