የጨረታ ማስታወቂያ
በጉለሌ ክ /ከተማ ወረዳ 10 የጄኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት እገልግሎት የሚውል
- ኦርጅናል ቋሚ ዕቃ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር (ኮንባይን ዴስከ) እስከ ጠረጴዛው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ሰለሚፈልግ
ተጫራቾች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው:: ተጫራቾች ይህንኑ የሚገልፅ ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ይዘው
- ጀምሮ ምዕራፍ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ ከሚገኘው በጉለሌ/ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የጀኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዕቃ ጥራት ያለው ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ ናሙና ማቅረብ ባለባቸው ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራች እቃዎችን ጋርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስማችሁን በመፃፍ ፊርማችሁንና አድራሻችሁን ማስፈርና ማህተም በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በጉለሌ ክ/ ከተማ ወረዳ 10 የምዕራፍ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ በመሚገኘው የጄኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ በ10ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበትበ10ኛው ቀን በ9፡30 ሰዓት በጄኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች በሰነድ የሰጡት ዋጋ መለወጥ መሻሻል ወይም ከውድድሩ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- የማወዳደሪያ ዋጋ ከቫት ጋር መጠቀስ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ብር 2000 (ሁለት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተመሰከረለት CPOማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሰሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡ -0989066757,0910355382,+251118234865,+251118231128
በጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 10
የጄኔራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት