የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2013
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት
- አላቂ የጽ/ህፈት መሳርያ፣
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ ፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- የህትመት ፣
- የመስተንግዶ ፣
- የኤሌትሮኒከስ እቃዎች ጥገና እንዲሁም
- የትራንስፖርት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና መጠቀም ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት፡
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ሊሆኑ ይገባል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆኑ ማስረጃ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- . በተቁ 1 እና 2 የተዘረዘሩ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ መወዳደሪያ ኦርጅናል ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- . የመወዳደሪያ ሰነዱን ስጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 4 ፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 አንድ መቶ ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ እንዲሁም ከስፔስፊኬሽንና ወይም ካቀረቡት ናሙና ውጪ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- .ተጫራቾች ለሚፈልጉት ጨረታ ሎት 1 አላቂ የጽህፈት ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ብር 5000 /አምስት ሺ ብር ብቻ | ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች ብር 2500 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/፣ ሎት 3 ለሰራተኞች የደንብ ልብስ 2000 /ሁለት ሺህ ብር/፣ የህትመት ስራዎች 1300/አንድ ሺህ ሶስት መቶ/፣የመስተንግዶ አቅርቦት፣213.60/ሁለት መቶ አስራ ሶስት ከስልሳ ሣንቲም/ የመኪና ትራንስፖርት አገልግሎት 1545.80. /ኣንድ ሺ አምስት መቶ አርባ አምስት ከሰማኒያ ሳንቲም/ ለኤሌክትሮኒክስ ጥገና 1400 አንድ ሺ አራት መቶ ብር በባንክ በተመሰከረለት CPO በጽ/ቤቱ አድራሻ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በሁለት ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ኦርጅናልና ኮፒ የጨረታ ሰነድ የሚል ጽሁፍ እንዲሁም የአቅራቢ ድርጅት ማህተም ሊሰፍርበት ይገባል፡፡
- . ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቹን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 የጨረታ ሳጥን 10ኛው ቀን እንድታስገቡ እያስታወቅን በዚሁ ቀን 8፡00 ላይ የሚታሸግ ሲሆን በእለቱ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቶች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መዋዋል አለባቸው:: በተጨማሪም ያሸነፉትን ዕቃዎች በ8 ቀናት ውስጥ ለፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል አጠናቀው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ቢፈጠር ከፊት ለፊቱ ፊርማ ሊኖረው ይገባል፡፡ አለበለዚያ የተሞላው ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የጨረታ ሰነዱ አንዱ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቶች ሊረዱት የሚገባ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተካተቱ ችግሮች ቢገጥሙ በግዥ መመሪያው የሚዳኝ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤታችን ለመግዛት ጨረታ ካወጣው ዕቃ 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ ይቻላል፡፡
- የትራንስፖርት ወጪ /የዕቃ መጓጓዣ/ በአቅራቢያው ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ፡- ናይጄሪያ ኤምባሲ ወደ ቀጨኔ መድኃኒዓለም በሚወስደው መንገድ ላይ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 4 ፋይናንስ
- ጽ/ቤት ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0111-26 69 36 | 0111550838 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በጉለሌ ክፍስ ከተማ የወረዳ 4 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት