የጨረታ ማስታወቂያ
በገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ ኮሚሽን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስር ተወርሰው የሚገኙ
- የተለያዩ አልባሳት፣
- የሞተር ሳይክሎች ፣
- ጫማዎች፣
- የመኪና መለዋወጫዎች ፣
- የመኪና ጎማዎች ፣
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ ዕቃዎች በጉሙሩከ ዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 67/2012 መሰረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በጨረታ ሰሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንሰ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቀበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ኢያይዞ በኤንበሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00-6፡30 እና ቅዳሜ 2፡00 እስከ 6፡00 የግልጽ እና የሃራጅ ጨረታ ሰነድ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅር/ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር /በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡት ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ 100,000.00 /አንድ መቶ ሺ ብር/ ለጨረታ ዋስትና የተረጋገጠ (CPO) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት መጫረት ይችላሉ፡፡
ተ.ቁ
የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስም
የጨረታው ዓይነት
የዕቃዎች ማመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
የጨረታው የመዝጊያ እና የመከፈቻ ቀንና ሰዓት
1
አዋሽ
የግልጽ ጨረታ
እስከ ታህሳስ 28/2013 ዓ.ም እስከ 3፡00 ስዓት
ታህሳስ 28/2013 ከ 3፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 4፡00 ሰዓትይከፈታል፡፡
የሃራጅ ጨረታ
እስከ ታህሳስ 27/2013 ዓ.ም ድረስ
እስከ ታህሳስ 27/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ይጀምራል ድረስ
- የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡- አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቶች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል ::
- ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል ።
- አሸነናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ ማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
- ከላይ በተቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
- ቅር/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ ፦
ተጫራቾች በእለቱ ኮሮናን ለመከላከል የሚጠቅሙ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በመልበስ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር በመያዝ እንድትገኙ እያሳሰበን ቅር/ጽ/ቤቱ ጨረታው የአካል እርቀትን በጠበቀ መልኩ በጥንቃቄ ለማድረግ ዝግጅት ያደረገ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-224-1402 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት