የጨረታ ማስታወቂያ
ኢንዶ/ግ/ዴ/02/2013
በአገር መከላከያ ሚ/ር መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ማቴሪያሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታች በሎት የተዘረዘሩትን ማቴሪያሎችን መግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከ6 ኪሎ ወደ ምኒሊክ በሚወስደው መንገድ ጃንሜዳ መግቢያው ፊት ለፊት በሚገኘው የመከላከያ ስፖርት ክለብ ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
- ሎት1. የጽሕፈት ማቴሪያል
- ሎት2. የጽዳት ማቴሪያል የሙዚቃ መሣሪያ መለዋወጫ
- ሎት3. የተለያዩ አልባሳት
- ሎት.4 የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ
ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የምስክር ወረቀት
- የቫት ሰርተፍኬት
- የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚገልፅ ወረቀት
- ቲን ነምበር እነዚህንና መሰል ተያያዥ ዶክመንት ሊኖሩት ይገባል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታኅሣሥ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል መሥሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116559081/0933815672
በአገር መከላከያ ሚ/ር መከላከያ
ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት