የጨረታ ማስታወቂያ
በጠቅላላ ግንባታ ስራ(G.C) ወይም በውሃ ግንባታ ስራ (WWC) ተቋራጮች በሙሉ
በጂማ ዞን የኦሞ ናዳ ወረዳ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት ለግብር እና ተፈጥሮ ሃብት ጽ/ቤት ከግብርና እድገት ፕሮግራም (AGP-II) ባገኘው የበጀት ድጋፍ በናዳ ቢዳሩ ቀበሌ ማኩሎ መስኖ ግንባታ ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚፈለገውን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል
- የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሰ የመንግስት ግብር የከፈለ እና መረጃ ማቅረብ የሚችል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን 1% በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለበት::
- 4 ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለበት ::
- ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ኦርጂናል እና ኮፒው ላይ በያንዳንዱ ገጾች ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በማኖር ማቅረብ አለባቸው ::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 300.00 ብር በመከፈል ከወረዳው ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት ማግኘት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተነገረበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በመቆየት በ25/2/2013 ዓ.ም 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
- አንድ ተጫራች በሌሎች ተጫራቶች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማስገባት አይቻልም ::
- የጨረታው መወዳደሪያ ሙሉ መስፈርት በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ውስጥ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ መረጃ ከወረዳው ኢ/ት/ጽ/ቤት ማግኘት ይቻላል ::
- ተወዳዳሪዎች ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከመሙላታቸው በፊት ቀበሌው ድረስ በመሄድ የግንባታውን ቦታ ማየት ሲኖርባቸው ለማየታቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ ስቁ 0471150170/0471150008/
የኦሞ ናዳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት