የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2013
በድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል እና በስሩ ላሉት ተቋማት ለ2013 በጀት ዓመት ለቢሮ የሚያገለግሉ አጠቃላይ ፅ/መሣሪያ ማወዳደር ይፈልጋል::
በጨረታው መወዳደር ለሚፈልጉ ተሣታፊዎች የጨረታ መስፈርት፡
- በዘርፉ የተሰማራ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያለው
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- የአቅራቢነት ሠርተፊኬት ያለው
- የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ወይም CPO ማስያዝ ይኖርበታል
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን ሠነዶች ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከተማ ስራ አስኪያጅ 1ኛ ፎቅ ግፋ/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛኑ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተገኙበት በከተማ ስራ አስኪያጅ 2ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 31 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሠነድ ላይ በአቅራቢነት መሞላት ያለበት ተሞልቶ የተጫራች ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም::
- የዋጋ ማቅረቢያ የሰነዱ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት
ማሣሰቢያ፡– ሠነዱ የጨረታ ተሳታፊዎች ዋጋ ለሰጣችሁበት በእያንዳንዱ ዕቃ ሳምፕል እንድታቀርቡ እያሳሰብን ሳምፕል ያልቀረበባቸው ዕቃዎች ግዢ የማናካሂድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆኘ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ የስ/ቁ 09 15 7553 24 ወይም 09 15 01 13 40
አድራሻ፡– (ትሪያንግል ሆቴል አጠገብ)
የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ቢሮ