Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others / Vehicle

በደ/ጎ/ዞን የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአ/ዘመን ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለመሰረተ ልማት አገልግሎት የሚውሉ ሮሎ፣ ግሬደር፣ ዶዘር፣ ሎደር፣ ሻውል ትራክ እና ገልባጭ መኪና የማሽን ኪራይ ግዥ ለመንገድ ጥገና በጥቅል ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ጎ/ዞን የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአ/ዘመን ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለመሰረተ ልማት አገልግሎት የሚውሉ

 • ሮሎ፣ ግሬደር፣
 • ዶዘር፣ ሎደር፣
 • ሻውል ትራክ እና ገልባጭ መኪና የማሽን ኪራይ ግዥ ለመንገድ ጥገና በጥቅል ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡
 1. በዘርፉ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው
 4. የግዥ መጠኑ ከ200000.00/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
 5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
 7. የሚገዙ የእቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፍኬሽን/ የማይመለስ 100 ብር ብቻ በመክፈል አ/ዘመን/ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአቅርቦት ዘርፍ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 17000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከቀን 9/2/2013 እስከ 29/2/2013 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን እንዲሁም ጨረታው ከቀን 30/2/2013 ዓ.ም ድረስ እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ፖስታ /የጨረታ ሰነዱን/ ማስገባ የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 30/2/2013 ዓ.ም 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙበት በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ሙሉ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058444 03 43/985 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
 12. ከቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ የስራ ቀን ከ2፡30 እስከ 11፡30 አሸናፊው ውል በፍትህ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 13. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሎትም ሆነ በተናጥል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ቢሆንም እያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር መሞላት አለበት፡፡
 14. የማሽን ነዳጅ፣ ዘይት እና የሎቪድ መጫኛ እንዲሁም ልዮ ልዮ ወጭዎችን በተጫራቹ /በባለሀብቱ/ የሚሸፈን ይሆናል/ተቋሙ የማይሸፈን/መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 15. የሚጫረቱበትን የማሽን ሊብሬና ቦሎ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
 • ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ 20 በመቶ ከፍ 20 በመቶ ዝቅ አድርጎ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • አሸናፊው ያሸነፋቸውን ማሽኖች በራሱ /በተጫራቹ/ ትራንስፖርት ወጭ እስከሚፈለገው ቦታ ድረስ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡

የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት