የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ጎ/ዞን የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአ/ዘመን አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ሎት 3.የሠራተኞች የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ፣ የተዘጋጁ ልብሶች ሸሚዝ፣ ካፖርት ፣ ቆብ፣ ዣንጥላ እና የኘላስቲክ ቦት ጫማ፣
- ሎት 4. ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፣
- ሎት 5. ልዮ ልዮ ህትመት ፣
- ሎት 6. አንዳንድ የተበላሹ ባውዛዎችን ጥገና ለማድረግ ስለፈለግን የመንገድ ዳር ባለ 250 ዋት ባጃጅ ባውዛ በጥቅል ዋጋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር
የሚችሉ በሆኑ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
- የሚገዙ የእቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፍኬሽን/ የማይመለስ 50 ብር ብቻ በመክፈል አ/ዘመን/ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአቅርቦት ዘርፍ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይምበጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥንጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከቀን 9/2/2013 እስከ 29/2/2013 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን እንዲሁም ጨረታው ከቀን 30/2/2013 ዓ.ም ድረስ እስከ3፡00 ሰዓት ድረስ ፖስታ /የጨረታ ሰነዱን/ ማስገባ የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 30/2/2013 ዓ.ም 30፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙበት በ4፡00 ሰዓትጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ሙሉ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 444 03 43/985 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ከቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ የስራ ቀን ከ2፡30 እስከ 11፡30 አሸናፊው ውል በፍትህ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- . መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሎትም ሆነ በተናጥል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ቢሆንም እያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር መሞላት አለበት፡፡
ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ 20 በመቶ ከፍ 20 በመቶ ዝቅ አድርጎ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ጥራቱ ከተጠበቀው በታች ከሆነ ንብረቱን የማንረከብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤታችን ንብረት ክፍል ድረስ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት