ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው መለያ ቁጥር 001/2013
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የየም ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት የ2013 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
ተቁ |
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ /Cpo/ |
1 |
አንድ |
የፅህፈት መሳሪያዎች |
10,000.00 ብር |
2 |
ሁለት |
የፅዳት መሳሪያ |
5000ብር |
3 |
ሶስት |
ኮምፒዩተርና የኤለክትሮኒክስ መሳሪያ |
3000ብር |
4 |
አራት |
የግንባታ /የሕንፃ መሳሪያ |
5000ብር |
5 |
አምስት |
የሰራተኞች ደንብ ልብስ |
5000ብር |
6 |
ስድስት |
የተሽከርካሪ ጥገና |
5000ብር |
7 |
ሰባት |
የተሽከሪካሪ ጎማ |
5000ብር |
8 |
ስምንት |
ፈርኒቸር |
5000ብር |
9 |
ዘጠኝ |
የእንስሳት መድኃኒት |
5000ብር |
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የሥራፈቃድና የዘመኑንየሥራግብር አጠናቀው የከፈሉበት ማስረጃ፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የንግድ መለያ ቁጥር (Tin number) ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የእንስሳት መድኃኒት ጨረታ ላይ መሳተፍ ያለባቸው ተጫራቾች የጅምላ አከፋፋይና በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን የሥራ ግብር አጠናቀው የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ተከታታይ ለ21 ቀናት የማይመለስ ለእያንዳንዱ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በመጨረሻው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ የም ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት በ21ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት በፋ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል ::
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ሁኔታ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ከተረጋገጠ በኋላ ወዲያውኑ ሌሎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ይመለሳል።
- .ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ከቫት ውጪና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ለይተው ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብና ዋጋ ላይ ስምና ፊርማቸውን ፣ቀንና የድርጅቱ ማህተም ማሳረፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ሙሉ በሙሉ በውሉ መሠረት ማጠናቀቃቸው ከተረጋገጠ በኋላ ሙሉ ክፍያ ይከፈላቸዋል፡፡
- የጨረታ መከፈቻው በበዓላትና በእረፍት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ላይ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉለውም፡፡
- በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ::
- ተጫራቾች የሥራ ፈቃዳቸው ያልተሟላ መረጃና የዋጋ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም፡፡
- የመወዳደሪያ ዘዴ በአይተም ይሆናል፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% መጨመር /ቀንሶ መግዛት መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተደራጁ አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት ተሻሽሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 172/2011 በደንቡ መሠረት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡
- . ጨረታውን ያሸነፈ አቅራቢ/አካል/ እስከ የም ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ሣጃ ድረስ ዕቃውን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የመወዳደሪያ ቋንቋ በአማርኛ ሲሆን የሚፈልገውን ዝርዝር ዕቃ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
- የየም ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ሣጃ ከተማ ሲሆን ከአ/አ 240 ኪሜ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ ላይ እንገኛለን፡፡
- ደንብ ልብስ፣ ቦርሳዎች፣እስክሪብቶ፣የኮምፒዩተር ወረቀት ሱመን እና የአጀንዳዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0474518006 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/የየም ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት