የጽ/መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃ ግዥ
ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቀጥር 05/2012
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ የአማሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መ/ ቤቶች በ2013 በጀት ዓመት
- ጽ/መሣሪያና
- ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታ ለመሳተፍ መሟላት የሚገባቸው ነጥቦች፡–
- የዘርፍ ንግድ ፈቃድ የዘመኑ ግብር ተከፍሎ የታደሰ ፣ ቲን ቁጥር ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫቲ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያለውና የሚያቀርብ፣
- ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ አ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር -8፣
- ተፈላጊ ጽ/መሳሪያና ሌሎች አላቂ ዕቃ የሚያቀርብበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያ ፕሮፎርማ ሞልቶ ከተፈላጊ መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ጋር በፖስታ አሽጎ የሚያቀርብ፣
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 አ/ወ/ገ/ባ/ሥ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ጨረታ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 14ኛ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 መውሰድ ይቻላል።
- ጨረታ ሣጥን የሚታሸግበትንና የሚከፈትበትን ዕለት በተመለከተ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ወደ ፊት የሚቆጠር በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ታሽገው በዕለቱ በ3፡15 ደቂቃ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በሳምንት ዕረፍት ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱ ይፋ ከሆነበት ዕለት ጀምሮ ለ7 የሥራ ቀናት ለቅሬታ አቤቱታ ጊዜ ሰጥቶ ከ8ኛው እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውል ካልተፈራረመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለመንግሥት ውርስ በማድረግ ለአፈፃፀሙ ለክልል ግዥ ኤጀንሲ ሪፖርት እናደርጋለን።
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ የሚያስይዝ መሆን አለበት።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ ሁሉንም ወጪ ችሎ እስከ አማሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መጋዝን አቅርቦ ማስረከብ አለበት።
- ለናሙና በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጠየቁት አሸናፊ ከፍ ያለ ዋጋ ያቀረበ ቢሆንም ትክከለኛና 1ኛ ደረጃ ያቀረበ አሸናፊ ይሆናል፣
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ በኳሊቲ 1ኛ ደረጃ መሆን አለበት። አቀላቅሎ የሚያቀርብ ካለ እንደተጨበረበረ ተቆጥሮ በክልል ግዥ ኤጀንሲና በህግ ዕርምጃ እንዲወሰድበት ይደረጋል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-046-457-05-15/09-16-06-83-30/09-16-13-00-84
አ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት