የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ቴክኒከና ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒከና ሳተላይት ኢንስቲትወት ውስጥ የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ ስራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት፡
- ደረጃቸው GC/BC5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
- ፍቃዳቸውንና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምዝገባ ሰርተፍኬታቸውን ለ2012 ዒ.ምያሳደሱየግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- ተጫራቾች ለስራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት_የአርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትውት ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 300,000 /ሦስት መቶ ሺ ብር/ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን የቴክኒካል እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡ 00 ሰዓት ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው::
- ጨረታው በ22ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ይታሸግና በዚያው እለትከቀኑ 8፡30ሰዓትተጫራቾች ወይምህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከናወን ይሆናል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
መረጃ ስልክ ቁጥር 046 881 06 94/0961 31-37-27/0912-06-24-38 አርባምንጭ
የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት አርባምንጭ ፖሊ ቴክኒክና ሳተላይት ኢንስቲትውት