Building Construction / Contract Administration and Supervision

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በጋሞ የአርባምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዙሪያ አጥር ግንባታን በ2013 በጀት ዓመት የግንባታ ሥራ ፍቃድ ያላቸውን ማህበራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በጋሞ የአርባምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዙሪያ አጥር ግንባታን በ2013 በጀት ዓመት የግንባታ ሥራ ፍቃድ ያላቸውን ማህበራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው Bc/Gc-9 በጀማሪ ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ ደረጃ የተደራጁ ማህበራት ሆነው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለ2012/2013 በጀት ዓመት የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ በክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ወይም በዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የተመዘገቡና የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ለ2012/2013 በጀት ዓመት ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የአቅራቢነት መረጃ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኦርጅናል ዶክመንታቸውን ለማመሳከሪያ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተቋራጮች አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችንና መሣሪያዎች በግላቸው አጓጉዘው የሚሰሩ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) 12,000.00 (አስራ ሁለት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዥ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም ጋራንት ተቀባይነት የለውም፡፡
  4. ተጫራቶች ሕጋዊ ፈቃዳቸውንና ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፊኬት በማቅረብ የጨረታወን ዶከመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 21 ተከታታይ ቀናት በአርባምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ግዥ ከፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከእርባምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ሂሳብና ከፍያ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 8 በመቅረብ በመከፈል የከፈሉበትን ወይም ገቢ ያደጉበትን ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታውን ሠነድ ከግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ::
  5. ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ በፊት የሥራሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ ማረጋገጥ ይኖርበታል::
  6. የፋይናንሻል ጨረታ ሰነዱ ዋጋ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፊከ ኮፒው በተለያየ ፖስታ በሰም ታሽጐ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት በሶስቱም ፖስታዎች ላይ ስም አድራሻና የፕሮጀክቱ ስም በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም በታሸገ አንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና እላይ በተዘረዘሩ ጽሁፎች እላዩ ላይ በመፃፍ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም እንደዚሁም በተ.ቁ 1 ላይ የተገለጹትን የህጋዊነት ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒው በተለያዩ ፖስታ ታሽጐ የጨረታ ማስከበሪያውን በኦርጅናል የፋይናንሻል ሰነድ ውስጥ በማስገባት ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ ላዩ ላይ ተጽፎበት በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ሁለቱንም ማለትም የህጋዊነት ሰነድ እና ፖስታዎችን በትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ ተከተው ከላይ በተገለጸው መሠረት ዝርዝር ጽሁፍ ተጽፎበትና በመፈረም እንዲሁም ማሕተም በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በአርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥና ንብረት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 13 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  7. የጨረታው ሳጥን የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል:: ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. የማንኛውም ተጫራች አርትሜትከ ቼክ ውጤቱ ከተነበበው ዋጋ ከ2% በላይና በታች ሆኖ ከተገኘ ከጨረታው ውጪ ይሆናል:: በተመሳሳይ ሪቨት /ቅናሽ ከ10% በላይ ማድረግም ከጨረታው ውጪ ያደርጋል::
  9. ነጠላ ዋጋ ከገበያ ዋጋ በታች ማቅረብ የጨረታውን ሂደትና ዋጋ ለማዛባት የሚደረግ ጥረት በመሆኑ በግዥ ሕጉ መሠረት እርምጃ ይወሰዳል ::
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው በተጨማሪም የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት አርባ

ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ