ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-0001
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ከደሳ–ሰላም፤ ከገንቡያ_መስቀልዝግባ ፤ ከደንገዝ–ዴባር ፤ እና ከዳሜ– ፈረዝጉራ የጠጠር መንገድ ስራ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
- GC/RC ደረጃ 9ኝና ከዛ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያላችሁ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፧ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በም/አ/ወ/ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት የማይመለስ 100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ/ፅ/ቤት ግዥ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በም/አ/ወ/ፋ/ፅ/ቤት ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የጨረታው ማስከበሪያው በኦሪጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሃያ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በሃያ አንደኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም።
- ጨረታው የሚከፈትበ ትን ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 011 343 91 73 ይደውሉ፡፡
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በጉራጌ ዞን የምሁርና
አክሊል ወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ዋና ጽ/ቤት