የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የጤና ቢሮ ከዚህ ቀደም ግንባታቸው ተጀምሮ ሳይጠናቀቁ ለቀሩት በጋሞ ዞን የዘፍኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቀሪግንባታ ሥራን፣
- በጎፋ ዞን የሳውላ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ ቀሪ ሥራን እና
- በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ሆስፒታል ማስፋፊያ ግንባታ ቀሪ ግንባታ ሥራን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት :-
- ደረጃቸው GC-5 /BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
- ፍቃዳቸውንና የከተማልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2012 ዓም ያሣደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት ጤና ቢሮ ፋይናንስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና 150,000 /አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን የቴክኒካል እና ፋይናንሻል አንድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት ቢሮው ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ መከተት አለባቸው።
- ጨረታው በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00-6፡00 ሰዓት በቢሮው ፋይናንስ ለዚሁ በተዘጋጀ ጨረታ ሳጥን በመክተት ይታሸግና በዚያው እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከናወን ይሆናል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-220-59-50/9208/5406/0232
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/ መንግሥት የጤና ቢሮ
/ሀዋሳ/