የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት መደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴ/መ/ቤቶች እንዲገዛ በጠየቁት መሠረት በየሎት ተጫራቾችን በመጋበዝ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት:
- ሎቱ 1. የቢሮ ጽ/መሣሪያ እና የቢሮ ጽዳት ዕቃ 2 የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማ ከነ ካናማናዳሪ
ስለዚህ መሳተፍ ሚችሉ ተጫራቾች፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ TIN ሠርቲፊኬት ያለው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ የአቅራቢዎች ምገባ ምስክር ወረቀት እና የግብር ግዴታቸውን ስለመወጣታቸው ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሠነድ ኦርጂናሉንና ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ያንዱን ዋጋበመጥቀስ በትከከል በመሙላት ሙሉአድራሻቸውን በመጻፍ እና ማህተም በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሠነድ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 15/ አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ቦኋላ ቀጥሉ የሚውለው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት በወላይታ ዞን የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ መ/ፋ/ዋና የሥራ ሂደት አደራሽ ይከፈታል። ከ15ኛው ቀን ቀጥሎ የሚውለው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ታሽጎ በዕለቱ ይከፈታል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በየሎቱ የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 /አስር ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ CPO በማስያዝ በጨረታው ፖስታ በመጨመር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጨራቾች የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይቻልም።
- ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማመልከቻ በመጻፍና ሣጥን ውስጥ በማስገበት ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችላሉ።
- በጨረታው ያሸነፈውን ዕቃዎችና አቅርቦቶችን ሳያንጠባጥብ በአንድ ጊዜ እስከ ወረዳው ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ወጪ ማቅረብ የሚችል።
- በጉዞ ወቅት የተበላሹና የተሰበሩ እንዲሁም የማይሰሩ ዕቃዎች ቢገኙ በራሱ ወጪ መሸፈን የሚችል። በአቅርቦትና ብቃት ጥራትና እንዲሁም ወቅታዊነቱ ከአሁን በፊት የተመሰከረለት ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- መ/ቤቱ እንዳስፈላጊነቱ ናሙና/ሳምፕል በሚፈልግበት ዕቃዎች ናመና/ሳምፕል ዕቃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በመንግስት ግዥ አዋጅ መሰረት 2% ለመከፈል የሚችል።
መ/ቤቱ የተሻላ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
መረጃ፡ ወላይታ ዞን የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ስልክ ቁጥር 046 272 03 36 መደወል ይቻላል።
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በወላይታ ዞን የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት