የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2013 በጀት ዓመት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚሆን ከዚህ በታች የተገለጹ የተለያዩ ግዢዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 2 የፈርኒቸር ዕቃዎች
- ሎት 3 ጀነሬተሮች
- ሎት 4 ሞተር ሳይክሎች
በመሆኑም፡
- ዘመኑን የታደስ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 10,000 (አስር ሺ) ብር እና ለሎት 2 ብር 5,000 (አምስት ሺ) ለሎት 3 ብር 4,000/አራት ሺ ፣ ለሎት 4 ብር 4,000/አራት ሺ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50 (ሃምሳ) ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናልና 1 ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ21ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0467710586/082/083
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ