የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ የስልጤ ዞን የወራቤ ማረሚያ ተቋም በ2013 በጀት ዓመት በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ለምግብ አገልግሎት የሚሆን
- በሎት አንድ (1) የተበጠረና ቅጭቅጭ የወጣለት ሰርገኛ፣ ጤፍ፣ በቆሎ፣ አተር፣ ፍርኖ ዱቄት፣ ባቄላ
- በሎት ሁለት (2) አንበሳ ሻይ ቅጠል፣ ስኳር፣ ጨው፣ ዘይት በፊት
- ሎት ሶስት(3) ጎመን ዘር፣ የተፈጨ በርበሬ፣ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ሞኮረኒ፣ ፓስታ፣ሩዝ፣ ምስር ክክ፣ አተር ከክ
- በሎት አራት (4) የማገዶ የባህር ዛፍ እንጨት ከሐምሌ1 /2012 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/04/2013 ዓ/ም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
በዚህም መሠረት፦
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና በአቅራቢያዎች ዝርዝር ውስጥ የተመደቡ
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ
- በሎት 2፣ ሎት 3 እና ሎት 4 ቫት VAT/ ወይም ቲኦቲ TOT/ ተመዝገቢ የሆና
- አሸናፊው ማንኛውንም ወጪ በራሱ ሸፍኖ ዕቃዎችን ወራቤ ማረሚያ ተቋም ቅጥር ግቢ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታው ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺ ብር) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እውቅና ያለው የፋይናስ ተቋም የተረጋገጠ ቼክ፣ ሌተር ኦፍ ክሬዲት፣ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ
- በጨረታው አሸናፊ የሚሆን ተጫራች በአሸነፉባቸው ዕቃ አይነቶች 10% ማስያዝ የሚችል
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት አቅርቦት በዘርፉ የማይመለስ ብር 50(ሃምሳ) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከግዥና ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውንና የመወዳደሪያ ሂሳባቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ እስከ 15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0467710108/25/318 መጠየቅ ይችላሉ።
የወራቤ ማረሚያ ተቋም