Building Construction / Contract Administration and Supervision

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የደቡብ ኦሞ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ የጤና አገልግሎት ግንባታዎች በ2013 የበጀት ዓመት አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ በከልሉ ጤና ቢሮ በተሰጠው ውክልና መሠረት ከዚህ ቀደም ተጀምረው ሳይጠናቀቁ የተቋረጡት ከዚህ በታች በሠንጠረዝ የተዘረዘሩትን የጤና አገልግሎት ግንባታዎች በ2013 የበጀት ዓመት ለማስገንባት ፡- በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ዮግዢ ዘዴ እያንዳንዱን ግንባታ በሠንጠረዥ በተገለጸው ደረጃ መሠረት በተናጥል አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ

የግንባታው ዓይነት

የግንባታው ቦታ

የተጫራች ደረጃ

የጨረታ ማስከበሪያ CP0 ብር መጠን

1

አልዱባ ፋርማሲ

በናፀማይ ወረዳ አልዱባ ቀበሌ

ጂሲ/ቢሲ ደረጃ ዘጠኝ እና ከዚያ በላይ ማህበራት ብቻ

20,000 / ሃያ ሺህ /ብር

 

2

ካንጋቴን ፋርማሲ

ኛንጋቶም ወረዳ ካንጋቴን ቀበሌ

ጂሲ/ቢሲ ደረጃ ዘጠኝ እና ከዚያ በላይ ማህበራት ብቻ

20,000 / ሃያ ሺህ / ብር

 

3

የመፀዳጃ ቤት

ደ/አሪ ወረዳ አይካመር ፤ የትነበርሽ እና ሜፅር ቀበሌ

ጂሲ/ቢሲ ደረጃ ዘጠኝ እና ከዚያ በላይ ማህበራት ብቻ

10,000 / አስር ሺህ / ብር

 

በዚህም መሠረት፡-

 1. በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፣ በክልሉ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ ለ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከላይ በሠንጠረዥ በተጠቀሰው ደረጃ መሠረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው
 2. በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እና ለ2013 ዓ,ም የበጀት ዓመት ስመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
 3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
 4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
 5. የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታደሰ የታከስ ከሊራንስ ሠርተፍኬት የያዘ Valid tax clearance certificate /
 6. በፈደራል ወይም በክልሉ የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን ከተሰጠው የሚመለከተው አካል በዘርፉ በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ / Registered in EPPA or PPA Suppliers List /
 7. በአደራጅ መ/ቤት ወይም ስልጣን በተሰጠው በሚመለከተው አካል ለ2013 የበጀት ዓመት የተረጋገጠ እና እውቅና የተሰጠው ማህበሩ የተሟላ አባል በመያዝ በትክክለኛ የማህበር ቁመና ላይ ስለመኖሩ እንዲሁም የ2013 ዓ.ም የሲኦሲ ምዝገባ ማስረጃ ያለው፣
 8. ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን የግንባታ ሥራ ውሎች በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረከብ ለመሆኑ፤ የግንባታ ጥራት ማጓደል ፤ ማዘግየት፤ ውል ማቋረጥ ወዘተ የውል አስተዳደርና አፈፃፀም ችግር የሌለበት ስለመሆኑ ስልጣን ከተሰጠው ከሚመለከተው የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር የመንግስት አካል ማስረጃ ያለው፤ በመሆኑም ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀከት ወስዶ በግንባታው ወይም ለፕሮጀከቱ የውል ስፔስፍኬሽን እና ማጠናቀቂያ ቀናት በሚፈለገው ጥራትና የማጠናቀቂያ ቀናት በማጠናቀቅ ለአሰሪው ባለ በጀት መ/ቤት ስወቅቱ ያላስረከበ ፤ ውል ያቋረጠ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፣ ለዚህም ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታው ውድድር በቀጥታ ውጭ ይደረጋል ወይም ይሰረዛል፡፡
 9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የግንባታው አይነት በሚጋብዘው ደረጃ መሠረት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችል በመሆኑ ህጋዊ የፅሁፍ ማመልከቻ ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 30 /ሰላሳ/ ተከታታይ ቀናት ከደቡብ ኦሞ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ከፍል የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
 10. ተጫራቾች መሳተፍ በፈለጉት ወይም በጨረታው ለወድድር በሚቀርቡት በመረጡት የግንባታ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በሰንጠረዡ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ከታወቀ ባንክ በሲ.ፒ.ኦ ብቻ በማዘጋጀት ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ ከጨረታው ቴክኒካል ኦርጂናል ዶክመንት ጋር በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
 11. ተጫራቾች አንድ ተጫራች ከአንድ ጨረታ በላይ መወዳደርና የመጫረቻ ሰነድ ማቅረብ የማይችል መሆኑን በሚገባ በማወቅ በራሳቸው ምርጫ በወደዱትና በፈቀዱት ለመረጡት አንድ ግንባታ ጨረታ ብቻ የጨረታ ሰነዱን በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴከኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ቴክኒካሉ ላይ ቴከኒካል ኦርጂናል እና ቴከኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ / ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በስላሳ አንደኛው /31ኛው/ ቀን (የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 6፡30 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቶች በሰም አሽገው በሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ካኪ ፖስታ ላይ በጥንቃቄ አስፈላጊውን መረጃ መግለፅ አለባቸው፡፡ የጨረታው አከፋፈት በሁለት መንገድ ሆኖ ቴክኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኋላ ፋይናንሽያል ዶክመንት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 • ተጫራቾች በምርጫቸው መሠረት የፈለጉትን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የሚችሉ ቢሆንም ነገር ግን ከአንድ በላይ የመጫረቻ ሰነድ ማቅረብና መወዳደር የማይችሉ እና ለውድድር የሚቀርቡት በአንድ ጨረታ ላይ ብቻ በመሆኑ ከአንድ በላይ ያቀረበ ተጫራች ሆን ብሎ የጨረታውን ሂደት ለማስተጓጎል የሚፈፀም ድርጊት መሆኑ ተመዝግቦ ከተሳተፈባቸው ከሁሉም ጨረታዎች በቀጥታ የሚሰረዝ እና በቀጣይም በሚወጡ ማንኛውም ጨረታዎች ላይ ላልተወሰነ ጊዜ እንዳይሳተፍ የሚታገድ ይሆናል፡፡
 • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0916-56-8283 ወይም 0467-75-31 -25 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር

የደቡብ ኦሞ ዞን ፋ/ኢ/ል/መምሪያ

ጅንካ