የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በደቡብ ኦሞ ዞን የኛንጋቶም ወረዳ መንግሥት ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡
- ሎት-1. የጽሕፈት መሣሪያ
- ሎት-2 ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት-3 የሠራተኞች የሥራ ደንብ ልብስ
- ሎት-4 ፈርኒቸር
- ሎት-5 ባለ ሁለት እግር ሞተር ሳይክል ሕጋዊ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል። በዚህ መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉና በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ በመንግሥት በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት/ቲን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 150/አንድ መቶ ሃምሳ ብር ከፍለው በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ከላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች ለተጠቀሰው ሥራ 5,000 /አምስት ሺ ብር/ በCPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማኖር ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ሰነድ በአግባቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የመ/ቤቱን ስምና አድራሻ እንዲሁም የግዥውን ዓይነት በግልጽ በኤንቨሎፕ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ፖስታውን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብቻ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤ በ16ኛው ቀን ፖስታው ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚሁ ዕለት ልክ ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኛ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት በመንግሥት ፋይናንስ ዋና የሥራ ሂደት በግዥና ንብረት አስተዳደር ኬዝ ቲም የሥራ ክፍል በግልጽ ይከፈታል። በ16ኛው ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሠነድ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው 20% /ሃያ በመቶ/መቀነስ ወይም መጨመር የሚችል ይሆናል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0911254974/0919634137
ደቡብ ኦሞ ዞን ኛንጋቶም ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት