ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መንግስት በጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የቡታጅራ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት
- የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና
- የተሽከርካሪ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ይጋብዛል።
- ተጫራቹ ለ2013 ዓ.ም የሚያገለግል የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ ቫት ሬጅስትሬሽን፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት የሚቻል ሲሆን የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎችን ሙሉ ስፔስፊኬሽን በዚሁ የጨረታ ሰነድ መመልከት አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በተዘጋጀላቸው የጨረታ ሰነድ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመስሪያ ቤቱ በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተወዳደሩበት ዋጋ ድምር ከ1%ያላነሰ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ አያይዞ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የሚያስገቡት የጨረታ ዋጋ ቫት ( VAT ) ጨምሮ መሆኑንና አለመሆኑን በግልጽ ካልተቀመጠ የቀረበው ዋጋ ቫት (VAT ) ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ16ኛው ቀን በ5፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስሪያ ቤታችን በሚገኘው ቢሮ ቁጥር 9 የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ተከፍቶ አሸናፊው የሚለይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ (የሕዝብ በዓል) ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት የቡታጅራ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ አጓጉዘው በማቅረብ ገጣጥመው ማስረከብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል ::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0461150110 እና 0461151323 ደውሎ ማረጋገጥ ይቻላል፡፡
የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በጉራጌ
ዞን የቡታጅራ ከተማ የመጀመሪያ
ደረጃ ፍ/ቤት